M.A.D Technologies PLC Vacancy 2026 | Outdoor Sales Agent (JEMLA) | የውጭ ሽያጭ ወኪል
M.A.D Technologies PLC, operating the JEMLA B2B e-commerce platform, invites qualified and motivated applicants for the position of Outdoor Sales Agent in Addis Ababa, Ethiopia.
M.A.D Technologies PLC የጅምላ (JEMLA) B2B ኢ-ኮመርስ መድረክን በማንቀሳቀስ ላይ ያለ ኩባንያ ሲሆን፣ ብቁ እና ተነሳሽነት ያላቸውን አመልካቾች ለውጭ ሽያጭ ወኪል (Outdoor Sales Agent) ሥራ አዲስ አበባ ውስጥ ይፋ አድርጓል።
JEMLA is a B2B e-commerce platform that provides fast-moving consumer goods (FMCG) to retail businesses including kiosks, hotels, restaurants, cafés, offices, and more. We offer competitive pricing and free delivery within 24 hours. Beyond product supply, JEMLA supports merchants with market insights, credit services, and digital financial services to help them run their businesses more effectively.
ጅምላ ለችርቻሮ ነጋዴዎች ኪዮስኮች፣ ሆቴሎች፣ ምግብ ቤቶች፣ ካፌዎች፣ መሥሪያ ቤቶችና ሌሎችም ፈጣን ተንቀሳቃሽ የሸቀጥ ዕቃዎችን (FMCG) በተወዳዳሪ ዋጋ እና በ24 ሰዓት ውስጥ በነጻ ማጓጓዣ በቀላሉ የሚያቀርብ የB2B ኢ-ኮመርስ መድረክ ነው። ኩባንያችን ከምርት አቅርቦት ባሻገር፣ ነጋዴዎች ንግዳቸውን የበለጠ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲያካሂዱ የገበያ መረጃዎችን፣ የብድር አገልግሎትን እና ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቶችን ይሰጣል።
The Outdoor Sales Agent serves as the face of JEMLA in the marketplace. The primary objective of this role is to engage directly with business owners, convert them into active JEMLA customers, collect customer data, attract new businesses, and ensure they become regular users of the platform.
የውጭ ሽያጭ ወኪሉ በገበያው ውስጥ የጅምላ ተወካይ ነው። የዚህ ሥራ ዋነኛ ዓላማ በገበያው ውስጥ በመንቀሳቀስ፣ የንግድ ባለቤቶችን በአካል በማናገር እና ንግዳቸውን ንቁ የሆኑ የጅምላ ደንበኞች በማድረግ፣ የደንበኞች መረጃ መሰብሰብ፣ አዳዲስ ንግዶችን መሳብ እና መደበኛ አዛዥ እንዲሆኑ ማድረግ ነው።
Identify and include potential customers within the assigned area. Conduct door-to-door visits and market scans to build and maintain a list of prospective customers.
በተመደበልዎ ቦታ ሊኖሩ የሚችሉ ደንበኞችን ለይቶ ማወቅና ማካተት፤ ከቤት-ወደ-ቤት ጉብኝትና የገበያ ቅኝት በማድረግ የወደፊት ደንበኞችን ዝርዝር መገንባትና መጠበቅ።
Introduce JEMLA's platform, order types, pricing, and delivery services to business owners. Register new businesses on the JEMLA platform and ensure registration information is accurately completed.
የጅምላን መድረክ፣ የትዕዛዝ ዓይነቶች፣ ዋጋና የማጓጓዣ አገልግሎት ለንግድ ባለቤቶች ማስተዋወቅ፤ አዳዲስ ንግዶችን በጅምላ መድረክ ላይ መመዝገብ እና የመመዝገቢያ መረጃዎች በትክክል መሞላታቸውን ማረጋገጥ።
Ensure newly registered businesses place their first order quickly. Follow up in person with registered businesses that have not yet ordered to resolve issues.
አዲስ የተመዘገቡ ንግዶች የመጀመሪያ ትዕዛዛቸውን በፍጥነት ማዘዛቸውን ማረጋገጥ፤ ከተመዘገቡ በኋላ ባላዘዙት ደንበኞች ዘንድ በአካል በመገኘት የማያዘዙበትን ምክንያት መፍታት።
Conduct regular field visits to existing customers to build strong relationships and encourage repeat orders. Promote additional JEMLA services including credit offerings and digital financial services.
ከነባር ደንበኞች ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠር፣ አስተያየት ለመሰብሰብ እና ተደጋጋሚ ትዕዛዞችን ለማበረታታት መደበኛ የField ጉብኝት ማድረግ፤ ተጨማሪ የጅምላ አገልግሎቶችን ማስተዋወቅ።
Track daily visits, new registrations, active customers, and sales volumes using JEMLA's field sales tools/CRM. Report market feedback and competitor activity to the Sales Manager.
ዕለታዊ ጉብኝቶችን፣ አዳዲስ ምዝገባዎችን፣ አክቲቭ የሆኑ ደንበኞችንና የሽያጭ መጠንን የጅምላን የField ሽያጭ መሣሪያዎች/CRM በመጠቀም መከታተል፤ የገበያ አስተያየቶችን ለሽያጭ ማናጀር ሪፖርት ማድረግ።
Interested applicants should apply through the following Telegram link:
አመልካቾች በሚከተለው የቴሌግራም ሊንክ በኩል ማመልከት ይችላሉ፡
Note: Applications are only accepted via the Telegram link above.
ማስታወሻ፡ ማመልከቻዎች የሚቀረቡት ከላይ በተጠቀሰው የቴሌግራም ሊንክ በኩል ብቻ ነው።
| Position Title / የሥራ መደብ | Company / ኩባንያ | Location / ቦታ | Employment Type / የሥራ ዓይነት | Experience / ልምድ | Application Link / የማመልከቻ ሊንክ |
|---|---|---|---|---|---|
| Outdoor Sales Agent / የውጭ ሽያጭ ወኪል | M.A.D Technologies PLC (JEMLA) | Addis Ababa / አዲስ አበባ | Full-time / ሙሉ ጊዜ | 1–2 years / 1-2 ዓመት | https://t.me/mad_tech_et |
📲 Get Daily Job Alerts
Join @EtcareersJobs for instant vacancy updates:
👉 https://t.me/EtcareersJobs